Quantcast
Channel: The Gulele Post
Viewing all articles
Browse latest Browse all 284

መሬት ለገባር

$
0
0

አቦይ የስልጣን ቁንጮ
ብሄር ነፃ አውጥተው
ህዝቡን ስለገዙት
በደደቢት በርሃ
እንዲሁም በአደይት
ደጅ የጠኑትን
በቅን እንዲገዙት
በጥይት ገዘቱት !!

በጠብመንጃ ሃይል
ልባቸው ደንድኖ
‹‹ብንቀጥን ጠጅ ነን››
እያሉ ፎከሩ
በውዥንብር ፋኖ
ህዝብ ማዕበል አለው
የዕውነተኞች ትንቢት
በግፈኞች ትዕቢት
አይቀርም ተዳፍኖ !!

የጅራፍ ግርፋት
የግፍ ፅኑ እስራት
ለኦሮሞ አርሶ አደር
የተማሪዎች ህልፈት
ዛሬ አይሆንም ፍርሃት …
ታሪክ አስተምሮታል
የወራሪዎች ዘመን
የኋሊት መሄዱን
የሴረኞች ብልሃት !!

የያዛቹት መሬት
ጠፍ መሬት አይደለም
ጠፍ የሚባል ድንበር
በምድር ላይ የለም
የቀጫቹት ትውልድ
ግፍ በደሉ በዝቷል
መሬት ልግባር ነው
ተብቃቁ ይብቃቹ
በቅቷል የናንተ አለም…

በኦሮሚያ መሬት ላይ
ዛሬ እንደ ትላንቱ
በነፍጥ ጦርነት
ልክ እንደጥንቱ
ሰረግ ወይ ጉተራ
እንደ መሬት ተዘካር
መሬት ልገባር
ስደት ለአስገባሪ
ገብር አቦይ ገልቱ!
***************
ገጣሚ፥ ኤበ ጮቆርሳ


Viewing all articles
Browse latest Browse all 284

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>